አሜሪካ የጣለችው የጉዞ ዕገዳ የአማራ ልዩ ኃይልንና የህወሃት አባላትን እንደሚያካትት አስታወቀች፡፡

በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ እንዳስታወቀው አገሪቱ በኢትዮጵያ ባለስልጣናት ላይ የጣለችው የጉዞ ክልከላ፣ የአሁንና የቀድሞ የኢትዮጵያም ሆነ የኤርትራ ባለስልጣትን ጨምሮ የህወሃትና የአማራ ልዩ ሃይሎችን ያካትታል ብሏል።

ከዚህ በተጨማሪም በጦርነቱ ውስጥ ተሳታፊ የሆኑ የፀጥታ አካላትን እንደሚያካትት ታውቋል።

ነገር ግን ከእነዚህ ከተጠቀሱት አካላት ውጭ ለትምህርት፣ ለስራና ለሌሎችም ጉዳዮች ወደ አሜሪካ የሚሄዱ ዜጎችን እንደሚያስተናግድ ኤምባሲው አስታውቋል።

በትግራይ ክልል ያለው አለመረጋጋት እንደሚያሳስበው የገለፀው ኤምባሲው ችግሩ ርሃብን ያስከትላል የሚል ስጋት እንዳለውም አስታውቋል።

የባይደን አስተዳደር በኢትዮጵያ ባለስልጣናት ላይ የጉዞ እገዳ መጣሉን ተከትሎ በመላው አለም የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ተቃውሟቸውን እያሰሙ ይገኛሉ።

አሜሪካዊዉ ሴናተር ጂም ኢንሆፍም ከኢትዮጵያ ጎን ሆነው ውሳኔውን ኮንነውታል ።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በአባቱ መረቀ
ግንቦት 24 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *