የትግራይ ክልል ሰላምና ደህንነት እንዲጠበቅ ጊዜያዊ አስተዳደሩ የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ ቢሆንም፣ የፌደራል መንግስት እንዲሁም የተለያዩ የሰብዓዊ ተቋማትና የመላው ኢትዮጲያዊን እገዛ ከሌለ በክልሉ ያለውን የቀደመ ሰላም በቅርቡ ለመመለስ እንደሚያስቸግር የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ምክትል ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር ሙሉቀን ሀፍቱ ለኢትዮ ኤፍኤም ተናግረዋል፡፡
በትግራይ ክልል ያለዉ ችግር የሁሉም ኢትዮጲያዊያን ችግር ነው ያሉት ዶ/ር ሙሉቀን፣ በተለይም ይህንን ችግር ለመቀልበስ ጊዜያዊ አስተዳደሩ ብቻ መፈታት እንደማይችልና ይልቁኑም መላው የኢትዮጲያ ህዝብ ከትግራይ ህዝብ ጎን ሊሆን እንደሚገባ አስታውቀዋል፡፡
የክልሉን የፀጥታ ጉዳይ ለማሻሻል ፤በክልሉ የተጎዱና የተፈናቀሉ ዜጎችን ለመደገፍ እንዲሁም የወደሙ ንብረቶችን ወደ ቀደመ ሁኔታቸው ለመመለስ ሁሉም ኢትዮጲያዊ ዜጋ የበኩሉን ሊወጣ እንደሚገባ ነው የጠየቁት፡፡
በትግራይ በአሁኑ ሰዓት አንፃራዊ ሰላም መስፈኑን ለኢትዮ ኤፍ ኤም ያስታወቁት የጊዜያዊ አስተዳደሩ ምክትል ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር ሙሉቀን፣ ይህንን አንፃራ ሰላም ለማስጠበቅና የክልሉንም የፀጥታ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ ለመመለስ ዘላቂ መፍትሄ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡
ይህን እዉን ለማድረግ ግን የሁሉንም ድጋፍ ትብብር ይጠይቃል ብለዋል፡፡
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በየዉልሰዉ ገዝሙ
ግንቦት 25 ቀን 2013 ዓ.ም











