ቻይና ለአለም ሀገራት የለገሰችው የኮሮና ቫይረስ ክትባት ቁጥር 350 ሚሊዮን ዶዝ ሆኗል

ቻይና በውጭ ጉዳይ ጽ/ቤት ቃል አቀባይዋ በኩል እንዳስታወቀችው፤ እስካሁን ድረስ ለቫይረሱ መድሃኒት የሚሆን ለአለም ሀገራት ያበረከተቻቸው የክትባቶች ቁጥር ከ350 ሚሊዮን በላይ መሆኑን ገልጻለች፡፡

ክትባቶቹን ሀገራችንን ጨምሮ 80 ለሚሆኑ የአለም ሀገራት የለገሰች ሲሆን 40 ለሚሆኑት ደግሞ የማጓጓዝ አገልግሎቶችንም ጭምር መስጠቷንም እንዲሁ አስታውቃለች፡፡

ቻይና ባሳለፍነው የመጋቢት ወር 300 ሺህ የሚሆኑ የኮቪድ-19 ክትባቶችን ለኢትዮጵያ መለገሷ አይዘነጋም፡፡

ወደፊትም ክትባቶችን ኢትዮጵያን ጨምሮ ክትባቶቹን በቀላሉ ማግኘት ለማይችሉ የአለም ሀገራት መለገስ ብቻም ሳይሆን ክትባቶችንም የመማጓጓዝ ስራዋን አጠናክራ እንደምትቀጥል ገልጻለች፡፡

በቻይና ስርጭቱን ከጀመረ ከአንድ አመት በላይ ያስቆጠረው ቫይረሱ ይህ ዘገባ እስከተዘገበበት ሰዓት ድረስ በአለም አቀፍ ደረጃ በቫይረሱ መያዛቸው በምርምራ የተረጋገጡ ሰዎች ቁጥር 171 ሚሊዮን የደረሰ ሲሆን በቫይረሱ ሕይወታቸው ያጡ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 3.5 ሚለዮን መድረሱን ሲ.ጂ.ቲ. ኤን ዘግቦታል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
ጅብሪል መሐመድ
ግንቦት 25 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *