ከጎርፍ በተጨማሪ የክረምት ወቅትን ተከትለዉ የሚከሰቱ አደጋዎች ተጋላጭ የሆኑ አከባቢዎችን መለየቱን የብሔራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

ከብሔራዊ ሜትሪዮሎጂ ኤጂንሲ በተገኘ መረጃ መሰረት እስከ ግንቦት 30 ድረስ ዝናቡ ይቀጥላል ብሏል፡፡

ክልሎችም የቀድመ ዝግጅት ከማድረግ በተጨማሪ የመከላከል ስራው ላይም በርትተው እንዲቀጥሉ መረጃዎችን እግር በእግር እያስተላለፍን ነው ሲሉ የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ዳሬክተር አቶ ደበበ ዘውዴ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

አቶ ደበበ አክለዉም ኮሚሽኑ እንደ ሀገር እና እንደ ክልል የጎርፍ ግብር-ሀይል አቋቁሞ ወደ ስራ መግባቱን ነግረዉናል፡፡

በቀጣዩ የዝናብ ወቅትም የጎርፍ አደጋ ያሰጋቸዋል ተብለው ከተለዩት ውስጥም የኦሮሚያ ፤የአማራ ፤የትግራይ ፤የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ፤የቤኒሻንጉል ጉምዝ እንዲሁም የሀረሪ ክልል እና ሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች አዲስ አበባ እና ድሬዳዋ መሆናቸውን አቶ ደበበ ለኢትዮ ኤፍ ኤም አስታውቀዋል፡፡

የኦሮሚያ ፤የአማራ ፤የደቡብ እና የትግራይ ክልል ደግሞ ከጎርፍ አደጋ ጋር በተያያዘ የመሬት መሸራተት እና መሰንጠቅ አደጋ ሊገጥማቸው እንደሚችል ጠቋሚ መረጃ ተገኝቷል ነዉ ያሉት፡፡

ኮሚሽኑ እንዳለው አስቀድሞ በደረሰው መረጃ መሰረት ከክልሎች ጋር ለችግሩ ተጋላጭ ከሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር በመሆን ከየካቲት እስከ መጋቢት ባሉት ወራት ውስጥ የተጠናከረ የታፋሰስ ስራ መሰራቱን አንስቷል፡፡

ይህ የተፋስስ ልማት ደግሞ የጎርፍ አደጋውን ከመከላከሉም በላይ ለዘላቂ ልማት እና ድርቅን በመከላከሉ ረገድ ትልቅ ፋይዳ እንዳለዉ አቶ ደበበ ተናግረዋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በያይኔአበባ ሻምበል
ግንቦት 25 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.