የከተማ አስተዳደሩ ለቅርስ እንክብካቤና ጥገና የሚያስፈልገዉን በጀት ባለመልቀቁ ታሪካዊ ቅርሶች አደጋ ተጋርጦባቸዋል ተባለ

የከተማው ባህል ፤ኪነ ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ እንዳለው የቅርስ ጥገና በጀት ስላልተለቀቀልኝ ጥገና ማድረግ አልቻልኩም፤ በዚህም የተነሳ በከተማ አስተዳደሩ ይዞታ ስር ያሉ ታሪካዊ ቅርሶች አደጋ ላይ ወድቀውብኛል ሲሉ የአዲስ አበባ ባህል ኪነ ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ የቅርስ ጥገናና እንክብካቤ ዳይሬክተር አቶ ደረጀ ስዩም ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

የአፄ ምንሊክ ቤተመንግስት፤ የወልደ ጻዲቅ ጎሹ እንዲሁም የሼህ ወጃሌ ቤቶች አደጋ ላይ ከወደቁ ቅርሶች መካካል መሆናቸውንም ኃላፊ ነግረውናል፡፡

ከቅርሶቹ በተጨማሪም በከተማዋ የሚገኙ የተለያዩ ሃዉልቶችም በዚህ አመት እድሳት እንዳልተደረገላቸዉ ገልጸው የከተማ አስተዳደሩ ለእነዚህ ቅርሶች ተገቢዉን ድጋፍ እንዲያደርግ ዳይሬክተሩ አሳስበዋል፡፡

ከመንግስት በተጨማሪም ሁሉም ህብረተሰቡም ቅርሶቹን መንከባከብ እንዳለበትም አቶ ደረጄ አሳስበዋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
አባቱ መረቀ
ግንቦት 25 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *