የ16 ቢሊዮን ብር ብድር ለንግድ ማህበረሰቡ መዘጋጀቱ ተገለጸ፡፡

የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል እንደተናገሩት፣
በሀገሪቱ በአጠቃላይ 2 ነጥብ 4 ሚሊዮን የንግድ ተቋማት ሲኖሩ 632 ሺህ 218 ያህሉ በአዲስ አበባ የሚገኙ ናቸው፡፡

ለጥቅል ሀገራዊ ምርቱ የንግድ ዘርፉ 28 በመቶ ያህል ድርሻ አለው ብለዋል፡፡

ከዚህ ቀደም ለ62 አመታት ያህል ያልተሻሻለው የንግድ ህግ በዘርፉ ማነቆዎች እንዲኖሩ ያደረገ መሆኑን ያስታወሱት ሚኒስትሩ፣ ከ34 አመታት ጥረት በኋላ በ2013 የተሻሻለው የንግድ ህግ መጽደቁን አንስተዋል፡፡

ይህም ወቅቱን የዋጀ እና ዘርፉን የሚያነቃቃ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

በንግድ ዘርፉ እየተካሄደ ያለው ሪፎርም የንግዱ ማህበረሰብን የሚያበረታታ እና የሚነሱ ችግሮችን እየፈታ የሚሔድ ነው ያሉት አቶ መላኩ ከብድር ፤ ከመሬት እና መሰረተ ልማት ጋር የተያያዙ ችግሮች ላይ የመፍትሄ አቅጣጫዎች መቀመጣቸውን አንሰተዋል፡፡

አቶ መላኩ በብድር አቅርቦት ረገድም ባለፈው አመት 8 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ተመድቦ እንደነበር ጠቅሰው በቀጣይ ለንግዱ ማህበረሰብ የሚሰጥ የ16 ቢሊዮን ብር ብድር ከልማት ባንክ ጋር መመቻቸቱን ተናግረዋል፡፡

በዳዊት አስታጥቄ
ግንቦት 25 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *