ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በክልሉ በግመል ላይ የታየው ምንነቱ በደንብ ያልታወቀ ወረርሽኝ መከሰቱን የሶማሌ ክልል የአርብቶ አደርና ገጠር ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጠይብ አህመድኑር ተናግረዋል፡፡
ሃላፊው እንዳሉት ወረርሽኙ ከእንሰሳት ወደ ሰው የሚተላለፍ መሆኑ እና አለመሆኑን ስላልታወቀ ህብረተሰቡ የግመል ስጋና ወተት ሲጠቀም ጥንቃቄ እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቧል።
ተመሳሳይ ምልክት ያለው የእንስሳት በሽታ በኬንያና በአንዳንድ የኦሮሚያ አካባቢዎችም መታየቱን ቢሮ ጠቁሟል።
የዚህ አዲስ ያልታወቀው በሽታ ናሙና ተወስዶ በፌዴራል ደረጃ በላብራቶሪ እየተመረመረ መሆኑንና በሶስት ወራት ጊዜ ውስጥ ምላሽ እንደሚሰጥ የሶማሌ ክልል የአርብቶ አደርና ገጠር ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጠይብ አህመድኑር ማስታወቃቸውን ከክልሉ ኮምዮኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን
ግንቦት 26 ቀን 2013 ዓ.ም











