ከ 25 ሚሊዮን ዶላር በላይ ወጪ የሚጠይቀው የሶዶ ክርስቲያን ሆስፒታል የማስፋፊያ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ።

የሶዶ ክርስቲያን አጠቃላይ ሆስፒታል የስፔሻሊቲ ሰርቪስ ማእከል የማስፋፊያ ግንባታ ለማከናወን የሚያስችለውን የመሰረት ድንጋይን በዛሬው እለት አስቀምጧል።

ከተመሰረተ አስራ ስድስት ዓመታትን ያስቆጠረው የሶዶ ክርስቲያን አጠቃላይ ሆስፒታል የስፔሻሊቲ ሰርቪስ ማእከል የሆነውን የማስፋፊያ ግንባታን ለማከናወን የመሰረት ድንጋይ አስቀምጧል።

የመሰረት ድንጋዮን በዛሬው እለት የጤና ሚኒሰትር ዶ/ር ሊያ ታደስን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የፌደራልና የክልል ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም የሆስፒታሉ ባለቤቶችና ሰራተኞች በተገኙበት የመሰረት ድንጋዩን የማስቀመጥ መርሃ ግብር ተከናውኗል።

ሆስፒታሉ በ 25 ሚሊዩን ዶላር ወጪ የሚገነባ ይሆናል ተብሏል።

የሶዶ ጠቅላላ ሆስፒታል ከዚህ ቀደም የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች በማስፋፋትም አሁን በሚገነባው የስፔሻሊቲ ሰርቪስ ማእከል ህንፃው የካንሰር፣ የእናቶችና ህፃናት፣ እንዲሁም በስፔሻሊስት ሃኪሞች ስልጠና፣ በአጥንት ስፔሻሊስት፣ እና ሌሎችም የሚሰጣቸውን የህክምና አገልግሎቶች የማስፋፋት አቅድ እንዳለው የሆስፒታሉ ዋና ስራ አስኪያጅ ኤፍሬም ገ/ስላሴን ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል።

ሆስፒታሉ በአሁኑ ሰዓት ከስድስት መቶ በላይ ሰራተኞች በስሩ ይገኛሉ።

በዓመት ከ 50 ሺ በላይ ህመምተኞችን የማገልገል አቅም ያለው ይህ ሆስፒታል በዛሬው እለት የመሰረት ድንጋይ የማስቀመጥ መርሃ ግበር የተደረገለት የእስፔሻሊቲ ሰርቪስ ማእከሉ ግንባታ ሲጠናቀቅም በዓመት ከ 1 መቶ ሺ በላይ ሰዎችን እንደሚያድግም ነግረውናል።

የሶዶ ክርስቲያን ሆስፒታል ከ 15 ዓመታት በፊት አሮን አዶልፍ በተባሉ አሜሪካዊ ሚሽነሪ የተቋቋመ የግል ድርጅት ነው።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በየዉልሰዉ ገዝሙ
ግንቦት 26 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.