ወጋገን ባንክ በወጋገን ይቆጥቡ ይሸለሙ በሚል ላካሄደዉ የሎተሪ እጣ መርሀ-ግብር አሸናፊዎች ሽልማታቸዉን ዛሬ አስረክቧል፡፡

ባንኩ ከጥቅምት አንድ እስከ መጋቢት 30 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ሲያከናዉነዉ ለቆየዉ የይቆጥቡ ይሸለሙ መርሃ-ግብር ነዉ ሽልማቱን የሰጠዉ፡፡

በዚህም መሰረት 1ኛ እጣ አንድ ዘመናዊ የቤት አዉቶሞቢል፣ 2ኛ እጣ ሁለት ባለ ሶስት እግር ተሸከርካሪዎች፣ የ3ኛ እጣ 20 የልብስ ማጠቢያ ማሽኖች እንዲሁም ኤል ኢዲ ቴሌቪዥኖችናን የሞባይል ስልኮችን ለባለእድለኞች አስረክቧል፡፡

የባንኩ ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ብርቱካን ገብረዝጊ፣ ባንኩ በአሁኑ ወቅት በመላዉ ሃገሪቱ በሚገኙ 397 ቅርንጫፎች ከሚሰጠዉ አገልግሎት በተጨማሪ የሞባይል ባንኪንግና የኢንተርኔት አገልግሎቶች፣በኤቲኤምና በክፍያ መፈጸሚያ ማሽኖች የክፍያ ካርድ አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡

ወጋገን ባንክ በአሁኑ ወቅት ከ2 ነጥብ 2 ሚሊዮን በላይ ደንበኞችና 4 ሺህ 56 ደንበኞች እንዳሉት ኢትዮ ኤፍ ኤም ከባንኩ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሰምቷል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በሙሉቀን አሰፋ
ግንቦት 26 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.