የእርስ በእርስ ግጭትን ይቀሰቅሳል የተባለው የቡሀሪ ጽሁፍ ከትዊተር ላይ እንዲጠፋ ተደርጓል፡፡

ትዊተር ይህንን ያደረኩት ፕሬዝዳንቱ የተቀመጠውን ህግ በመተላለፋቸው ነው ብሏል፡፡

የናይጄሪያው ፕሬዝደንት ሙሀሙዱ ቡሀሪ “….ሰርጎ ገቦች እና ወንጀለኞችን በማገዝ ሀገሪቱን ለማፍረስ ለሚፈልጉ እና የሚጥሩ ኃይሎችን ከዚህ በኃላ አንታገስም ”

የናይጄሪያ የማስታወቂያ ሚኒስትር የትዊተርን እርምጃ ኢ-ፍትሃዊ ፣ “ደብል ስታዳርድ” ነው ብለውታል ፡፡

ቢቢሲ እንዳስነበበው ከፕሬዝደንቱ የተላከ ትዊት ሲሰረዝ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው፡፡

የትዊተር ቃል አቀባይ ልኡክ ጽሁፉ “የትዊተርን ህጎች የጣሰ ነው ” ብለዋል።

መግለጫው ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ አልሰጠም ፡፡

ቡሃሪ በትዊተር ገፃቸው ላይ እርምጃ የሚወሰድበት አካል ወይም ቡድን ስም አልጠቀሱም ፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በያይኔአበባ ሻምበል
ግንቦት 26 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *