የእስራኤል ተቃዋሚ ፖርቲዎች ጥምር መንግስት ለመመስረት ከስምምነት ላይ ደረሱ፡፡

ይህ አዲሱ የእስራኤል ተቃዋሚ ፓርቲዎች ስምምነትም የቤኒያሚን ኔታንያሁን የ 12 ዓመታት የጠቅላይ ሚኒስትርነት ዘመን ማብቂያ አድርጎታል፡፡

የየሽ አቲድ ፓርቲ መሪው ያይር ላፒድ በስምንት ቡድኖች የተቋቋመ ጥምረት መመስረቱን አስታውቀዋል፡፡

በስምምነቱ መሰረትም ስልጣን በዙር የሚሰጥ ይሆናል ፡፡

በዚህ መሰረትም የቀኝ ክንፉ የያሚና ፓርቲው ናፍታሊ ቤኔት በቀዳሚነት ጠቅላይ ሚንስትር ይሆናሉ እንደ ቢቢሲ ዘገባ።

በቀጣይ ላፒድ ስልጣኑን እንደሚቀበሏቸው ተነግሯል።

መንግሥት ለመመስረት የሚያስችል ቃለ መሐላ ከመፈጸሙ በፊት ግን የፓርላማዉ ድምጽ ያስፈልጋል፡፡

ላፒድ በሰጡት መግለጫ ስለስምምነቱ ለፕሬዝደንት ሬውቨን ሪቭሊን ማሳወቃቸውን ገልጸዋል።

“ይህ መንግስት ሁሉንም የእስራኤል ዜጎች፣ የመረጡትንም ሆነ ያልመረጡትን ለማገልገል እንደሚሠራ ቃል እገባለሁ” ብለዋል፡፡

“ተቃዋሚዎቻቸውን የሚያከብር ሲሆን ሁሉንም የእስራኤልን የህብረተሰብ ክፍሎች አንድ ለማድረግ እና ለማገናኘት የቻለውን ሁሉ ያደርጋል” ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ህብረቱ በ 120 መቀመጫዎች ባሉት ክኔሴት (የእስራኤል ፓርላማ) የአብላጫውን ድጋፍ ማግኘት ካልቻለ ሃገሪቱ በሁለት ዓመታት ውስጥ ለአምስተኛ ጊዜ ምርጫ ለማካሄድ ትገደዳለች፡፡

ጥምረት የፈጠሩት ፓርቲዎች የእስራኤልን ፖለቲካ ሙሉ ገጽታ ያሳያሉ ተብሏል፡፡

ፓርቲዎቹ ኔታንያሁን ለመተካት ከማቀድ ውጭ በፖለቲካዊ ጉዳዮች ብዙም የሚያመሳስላቸው ነገር የለም፡፡

የእስራኤል መገናኛ ብዙሃን ሁሉም ሃሳቦች ተነስተው ከስምምነት አልተደረሰም፡፡

ይህም ጥምረቱ የመተማመኛ ድምጹን ያሸንፋል በሚለው ላይ ጥርጣሬ ጭሯል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በያይኔአበባ ሻምበል
ግንቦት 26 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.