የግብፅ የነዳጅ አገልግሎት መርከብ በቀይ ባህር ውስጥ ሰጠመች

አንድ የግብፅ ካፒቴን ህይወቱ አልፏል ፣ አንድ መሐንዲስ እስካሁን አልተገኘም ፣ 11 ሰዎች ደግሞ በህይወት መትረፍ ችለዋል፡፡

የነዳጅ ማመላለሻ መርከቧ በግብጽ ሱዌዝ ባሕረ ሰላጤ ውስጥ ከራስ ገሬብ ጠረፍ መስጠሟን የአካባቢው መገናኛ ብዙሃን ትናንት ዘግበዋል፡፡

የመርከቡ ካፒቴን ዮስሪ ሱልጣን ሁሉም የጀልባዋ ሰራተኞች በህይወት እስኪወጡ ድረስ አልወጣም ብሎ ሲታገል እንደ ሰጠመ ሚድል ኢስት ሞኒተር ዘግቧል፡፡

በግብጽ የጠረፍ ከተማ ሁርጋዳ የባህር ነፍስ አድን እና አካባቢ ጥበቃ ማህበር ሊቀመንበር ሃሰን አልታይብ መርከቧ ከራስ ጋሬብ ወደ ደቡባዊቷ የሲናይ ከተማ አቡ ዜኒማ እየቀዘፈች እንደነበር ተናግረዋል፡፡

መርከቧ ከሰጠመ ጀልባ ስብርባሪ ጋር መጋጨቱ ውሃ ወደ ውስጥ እንዲሰርግ በማድረጉ ለመስጠም እንደተገደደች አያይዘው ገልጸዋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በያይኔአበባ ሻምበል
ግንቦት 26 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *