በሱዳን ካርቱም መከላከያ ሚንስቴር ዋና መስሪያ ቤት ፊት ለፊት የተካሄደውን ጭፍጨፋ ሁለተኛ ዓመት ለማሰብ ተቋዋሚዎች አደባባይ ወጥተዋል፡፡

በሺዎች የሚቆጠሩ የዴሞክራሲ አቀንቃኝ ሰልፈኞች እ.ኤ.አ. ሰኔ 3 ቀን 2019 ዋና መሥሪያ ቤት ፊት ለፊት የተካሄደውን ጭፍጨፋ ሁለተኛ ዓመት በማስመልከት በመላው ካርቱም ሰልፍ አካሄደዋል ማካሄዳቸውን አናዶሉ ዘገቧል፡፡

ሰልፈኞቹ በጠቅላይ ሚኒስትር አብደላህ ሃምዶክ ቢሮ ፊት ለፊት ቆመው ከ128 በላይ ለተገደሉ ሰዎች ፍትህ እንዲሰጣቸው እና ለሰሩት ወንጀል በአስቸኳይ ተጠያቂ እንዲሆኑ ጠይቀዋል ፡፡

የሱዳን የባለሙያዎች ማሕበር የጠራው ነው የተባለው ይህ ሰልፍ በመላ ሀገሪቱ እየተቀጣጠለ ነው ተብሏል፡፡

የሱዳን ጦር የዛሬዉ ሠልፍ ከመጀመሩ በፊት ወደ መንግስት መስሪያ ቤቶች እና ወደ ጦር ሠፈሮች የሚወስዱ ዋና ዋና መንገዶችን ዘግቷል።

የጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ መንግስት ተቃዋሚዎችን እንደማይታገስ እና የኃይል እርምጃ እንደሚወስድ አሳስቧል ፡፡

መንግስት ግድያውን ለማጣራት ልዩ የምርመራ ኮሚቴ ማቋቋሞን ማስታወቁ የሚታወስ ነው፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በያይኔአበባ ሻምበል
ግንቦት 27 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.