የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የአልቃይዳ የሰሜን አፍሪቃ ክልል መሪ መገኛ ስፍራ ለጠቁም 7 ሚሊዮን ዶላር ሽልማት ይሰጣል ብሏል፡፡
አልጄሪያዊው አቡ ኡባይዳህ ዩሱፍ አል-አናቢ ፈረንሳይ በማሊ ባደረገችው የጦር ዘመቻ ወቅት የቀድሞው አብደልመልክ ድሩክዴል መሞታቸውን ተከትሎ ባለፈው ዓመት ህዳር ወር ላይ የተተኩት አሁን በእስላማዊው ማግሬብ የአልቃይዳ መሪ ናቸው።
ቡድኑ አሜሪካውያንን በመጥለፍ እና በመግደል ተጠያቂ ነው ተብሏል እንድ ቢቢሲ አፍሪቃ ዘገባ ፡፡
የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ እንዳሳወቀው አል-አናቢን እ.ኤ.አ. በ 2015 “በልዩ ደረጃ የተሰየመ ዓለም አቀፍ አሸባሪ” ብሎ የተዘረዘረ ሲሆን እ.ኤ.አ. በ 2016 በተባበሩት መንግስታት ማዕቀብ ዝርዝር ውስጥ ተካትቷል ፡፡
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በያይኔአበባ ሻምበል
ግንቦት 27 ቀን 2013 ዓ.ም











