የቻይና ኩባንያዎች በህዳሴው ግድብ ግንባታ ላይ እየተሳተፉ ቢገኙም የግብጽ እና የቻይናን ግንኙነት አያደናቅፍም ሲሉ አንድ ከፍተኛ የካይሮ ባለስልጣን አስታወቁ

የግብፅ የፓርላሜንታዊ የመከላከያ እና የብሔራዊ ደህንነት ኮሚቴ ሴክሬታሪ አህመድ አልአዋዲ ሰሞኑን በሰጡት አንድ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንዳሉት የቻይና ኩባንያዎች በህዳሴው ግድብ ግንባታ ላይ እየተሳተፉ ቢገኙም የግብጽ እና የቻይናን ግንኙነት አያደናቅፍም ብለዋል ፡፡

ሁለት የቻይና ኩባንያዎች የኢትዮጵያን “ታላቁ ህዳሴ ግድብ” የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ግንባታን ለማጠናቀቅ እየሰሩ እንደሆነ ይታወቃል፡፡

በጥቅምት (እ.ኤ.አ.) 2019 የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኢኮኖሚ ፣ ማህበራዊ እና አካባቢያዊ ተፅእኖዎች ዙሪያ በመከሩበት ወቅት የቻይና ኩባንያዎች በታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ስራ ላይ የቻይና ኩባንያዎች መሳተፋቸው የግብፅን ቅሬታ ለማስተላለፍ ከቻይና አምባሳደር ጋር ስብሰባም አዘጋጅተው ነበር ፡፡

ግብፅ እና ሱዳን በ ‹ግድቡ › ዙሪያ ቻይና እንድታደራድር ለማድረግ ሞክረዋል ፡፡

ቻይና ከሶስት ሀገሮች ጋር ግንኙነቷን ለማጠናከር እንደምትፈልግ ሀገራቸው የኢትዮጵያ ፤ የግብፅ እና የሱዳንም ወዳጅ ናት ሲሉ በኢትዮጵያ የቻይና ኤምባሲ የተልእኮ ምክትል ሃላፊ ኪ ቲያን ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት መግለጻቸው ይታወቃል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በያይኔአበባ ሻምበል
ግንቦት 27 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *