መንግስት ከቤት ንብረታችን በግድ ሊያፈናቅለን ነው ያሉ የእስክንድርያ ነዋሪዎች ለተቃውሞ አደባባይ መውጣታቸው ተሰምቷል

የግብጽ መንግስት ለባህረ ሰላጤ ሀገራት ባለሀብቶች መሬት ለመስጠት አቅዷል በሚል በመቶዎች የሚቆጠሩ አሌክሳንደሪያ ነዋሪዎች መሬታቸውን እንዲለቁ መደረጉን በመቃወም ነው ሰልፍ መውጣቸው የተሰማው፡፡

ባለፈው አርብ ደግሞ ከሰላት በኋላ የተቃውሞ ሰልፉን ብዙዎች ተቀላቅለው እንደነበር ያስታሰው ዘገባው፣ ከፖሊሶች ጋርም ግጭት ውስጥ ገብተዋል ሲል middle east eye ዘግቧል ፡፡

በግጭቱ በርካታ ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተሰምቷል

በሰላማዊ ሰልፉ ምክንያት ቤቶቹን የማፍረስ ሥራው ለጊዜውም ቢሆን ተቋርጦ እንደ ነበር ተነግሯል፡፡

ነዋሪዎቹ መንግስት ግልጽ የሆነ የካሳ እቅድ እንደሌለው በመግለጽ “አንሄድም” እያሉ በመጮህ ፤ ሰልፉን ሌሎችም አንዲቀላቀሉ እና አጋርነታቸውን እንዲያሳዩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ሰልፈኞቹ ከፖሊሶች ጋር መጋጨታቸውን ያስታወሰው ዘገባው ፖሊስም አስለቃሽ ጭስና የጎማ ጥይቶች ሰልፈኞችን ለበተን መጠቀሙ በዘገባ ተጠቅሷል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በያይኔአበባ ሻምበል
ግንቦት 30 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.