በሱዳን ዳርፉር ግዛት በተቀሰቀሰ የጎሳ ግጭት የ36 ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡

ከሟቾች በተጨማሪ በግጭቱ 32 ሰዎች መቁሰላቸውንም ሲጂቲኤን አፍሪካ ዘግቧል።

ግጭቱ የተከሰተው በደቡባዊ ዳርፉር በሚኖሩ ፌላታ እና ቴይሻ በተሰኙ ሁለት ጎሳዎች መካከል በተፈጠረ የመሬት ይገባኛል ግጭት እንደሆነ ዘገባው ጠቁሟል።

በሱዳን ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት እና በአካባቢው በሚንቀሳቀሱ አማጺ ሀይሎች መካከል የተለያዩ ስምምነቶች ቢደረጉም በአካባቢው ጎሳን መሰረት ያደረጉግጭቶች በተደጋጋሚ እየተከሰቱ እንደሆነ ተገልጿል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ግንቦት 30 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.