ከትግራይ ክልል የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ አገራቸው እንዲመለሱ እየሰራ መሆኑን በሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ገለጸ፡፡

ኤምባሲዉ እንዳለዉ ዜጎቹ ወደ አገራቸዉ እንዲመለሱ የሚደረገዉ በአካባቢው አስተማማኝ ሠላም በመስፈኑ ነዉ ብሏል፡፡

በሱዳን የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ባወጣው መግለጫ፣ ስደተኞቹ የመጡበት አካባቢ አስተማማኝ ሠላም የሰፈነ በመሆኑ ወደ አገራቸው የሚመለሱበትን ሁኔታ እያመቻቸሁ ነው ብሏል።

ኤምባሲው በማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገፁ ባወጣው መግለጫው፣ ከቀያቸው ተፈናቅለው በአገር ውስጥና በውጭ የሚገኙ ስደተኞች ወደ መደበኛ ኑሯቸው ለመመለስ መንግስት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ ገልጿል፡፡

በትግራይ ክልል በተካሄደዉ እና እየተካሄደ በሚገኘው ህግ የማስከበር ዘመቻ በርካቶች ወደ ሱዳን መሰደዳቸው የሚታወስ ነው።

UNICEF ባወጣው ሪፖርት መሰረት 1 ነጥብ 6 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች በግጭቱ ምክንያት ተፈናቅለዋል።

ባሳለፍነው ሳምንት ዓለም አቀፍ ተቋማት 90 በመቶ የሚሆኑ የትግራይ ክልል ነዋሪዎች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል ሲሉ ማስታወቃቸዉ አይዘነጋም፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በዳዊት አስታጥቄ
ግንቦት 30 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *