የኬንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አዲስ አበባ ገቡ፡፡

የኬንያዉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሪይቸል ኦማሞ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ መግባታቸውን የገለጸዉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ነዉ፡፡

ሚኒስትሯ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም የውጭ ጉዳይ ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ አቀባበል አድርገዋቸዋል፡፡

የኬንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሪይቸል ኦማሞ በአዲስ አበባ ቆይታቸው በሁለትዮሽና በቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በአባቱ መረቀ
ግንቦት 30 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *