ኤርትራ የህወሓት አመራሮችን ትደግፋለች ስትል አሜሪካ ላይ ክስ መሰረተች፡፡

የኤርትራ መንግስት አሜሪካ የህወሓት አመራሮችን ትደግፋለች ሲል ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታዉ ምክር ቤት ክስ ማስገባቱን አስታዉቋል፡፡

የአገሪቱ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳሌህ እንዳሉት፤ አሜሪካ ላለፉት 20 አመታት በላይ በትግራይ ክልልና በቀጠናዉ ጦርነት እንዲነሳ ስትሰራ ቆይታለች ብለዋል፡፡

አሁንም የባይደን አስተዳደር ቀጠናዉን ወደ ትርምስ ለማስገባት እየሰራ ይገኛል ሲሉ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ መናገራቸዉን አሶሼድ ፕረስ ዘግቧል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም የኤርትራዉ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳሌህ ዋሽንግተን በኢትዮጵያና በኤርትራ ባለስልጣናት ላይ የጣለችዉን የጉዞ እገዳ አግባብነት የሌለዉ ሲሉ ተችተዋል፡፡

የባይደን አስተዳደር እየሄደበት ያለዉ መንገድ ህወሓት ዳግም አንሰራርቶ ወደ ስልጣን እንዲመጣ በማሰብ እንደሆነም ኤርትራ ለፀጥታዉ ምክር ቤት በጻፈቸዉ ደብዳቤ ገልፃች፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በአባቱ መረቀ
ሰኔ 01 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *