በሚያዚያ ወር ብቻ 10 የኮንትሮባንድ ወንጀል መዝገቦች ውሳኔ ማግኘታቸው ተገለጸ፡፡

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ስምንተኛ ፣ አምስተኛ እና ዘጠነኛ ምድብ ወንጀል ችሎት በኮንትሮባንድ ወንጀል ተጠርጥረው ጥፋተኛ በተባሉ 10 የወንጀል መዝገቦች በሚያዚያ ወር ውሳኔ ማግኘታቸዉን ኢትዮ ኤፍ ኤም ከጠቅላይ አቃቤ ህግ ሰምቷል፡፡

በሚያዚያ ወር በዋሉት ስምንተኛ ፣ አምስተኛ እና ዘጠነኛ ችሎቶች ውሳኔ ካገኙት መዝገቦች መካከል በመዝገብ ቁጥር 286908 ፣ 286811፣ 286757፣ 287956፣ 283481፣ 289917፣ 287763፣ 28786፣ 283013፣ 288190 ተከሰዉ የነበሩ ሲሆን እያንዳንዳንዳቸው በአስር መዝገብ ከሁለት አመት እስከ አምስት አመት በሚደርስ እስር መቀጣታቸው ተገልጿል፡፡

በተጨማሪም በእያንንዳቸው ከ10 ሺህ ብር እስከ 75 ሺህ ብር የሚደርስ የገንዘብ መቀጮ የተጣለባቸው መሆኑን ኢትዮ ኤፍ ኤም ከጠቅላይ አቃቤ ህግ የኢኮኖሚ ወንጀል ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ያገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በረድኤት ገበየሁ
ሰኔ 02 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *