5 ግብጻዊያን በአይ ኤስ ታፈኑ፡፡

በግብጽ የሲና ፔንሱላ አካባቢ በትንሹ 5 ሰዎች በአይ ኤስ አይ ኤስ የሽብር ቡድን ታፍነው መወሰዳቸውን የሀገሪቷ የደህንነት ሃላፊዎች ይፋ አድርገዋል፡፡

ሰዎቹ ወደ መስሪያ ቦታቸው ቢር አል አበድ ከተማ በመጓዝ ላይ እንደነበሩ ድንገት የአይ ኤስ አባላት አስቁመዉ አፍነው እንደወሰዷቸው ነው ሃላፊዎቹ የገለጹት፡፡

ታፍነው ከተወሰዱት ውስጥ 3ቱ ኢንጂነሮች ፤ አንዱ አሽከርካሪ ሲሆን ሌላኛው ደግሞ የቀን ሰራተኛ ነበር ብለዋል፡፡

አይ ኤስ በግብጽ በተለይም የደህነንት ባለሙያዎች ላይ ያነጣጣረ ተደጋጋሚ ጥቃቶችን እየፈጸመ እንደሚገኝ አሶሼትድ ፕረስ ዘግቧል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በጅብሪል ሙሃመድ
ሰኔ 02 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.