ተገልጋዮች ፓስፖርት ለማግኘት በኦን ላይን ቀጠሮ ሲያሲዙ ጥንቃቄ እንዲደርጉ የኢሚግሬሽን ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ አሳሰበ

ኤጀንሲዉ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቀዉ ተገልጋዮች ፓስፖርት ለማዉጣት በኦን ላይን ቀጠሮ ሲያሲዙ ያልተሟላ መረጃን በመላክ በርካቶች እየተጭበረበሩ ነዉ ብሏል፡፡

የኢሚግሬሽን ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ደሳለኝ ተሬሳ ከጣቢያችን ጋር በነበራቸዉ ቆይታ ተገልጋዮች ፓስፖርት ለማግኘት በኦን ላይን ቀጠሮ ሲያሲዙ ጥንቃቄ እንዲደርጉ ሲሉ አሳስበዋል፡፡

የፓስፖርት አገልግሎት በኮቪድ 19 ምክንያት በኦንላይን መሰጠጥ መጀመሩን የገለፁት አቶ ደሳለኝ በዚህም ተገልጋዮች ወደ ተቋሙ ከመምጣታቸዉ በፊት በኦን ላይን ቀጠሮ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል፡፡

ይህንንም ተከትሎ ኢንተርኔት ካፌ አገልግሎት የሚሰጡ አካላት ኤጀንሲዉ የሚጠይቃቸዉን ሳያሟሉ ቀጠሮ እንደሚያሲዙም ተናግረዋል፡፡

በዚህም ተገልጋዮች ወደ ኤጀንሲዉ በመምጣት ቅሬታ እንደሚያቀርቡ የገለፁት ዳይሬክተሩ ይሁን እንጅ ችግሩ የኢንተርኔት ካፌዎቹ ችግሩ በመሆኑ ተገልጋዮች ተገቢዉን መስፈርት አሟልተዉ መላካቸዉን እንዲያረጋግጡ አሳስበዋል፡፡

ማንኛዉም ተገልጋይ ፓስፖርት ለማግኘት የታደስ የቀበሌ መታወቂያና አግባብነት ያለዉ የልደት ሰርተፊኬት በመያዝ ቀጠሮ ማስያዝ እንደሚጠበቅባቸዉ አቶ ደሳለኝ ተናግረዋል፡፡

ኤጀንሲዉ ከአገር ዉስጥ በተቸማሪም በተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶች ለሚገኙ ዜጎች የቪዛ እድሳትና አገልግሎት ከቪዲቸር ከተሰኘዉ ኩባንያ ጋር እየሰጠ እንደሚገኝም አስታዉቋል፡፡

አገልግሎቱን ለማግኘት ከዚህ ቀደም ተገልጋዮች 3 ወር ይብቁ እንደነበር ያስታወሱት አቶ ደሳለኝ አሁን ላይ ግን በ15 ቀናት ዉስጥ ባሉበት እንዲደርሳቸዉ ተደርጓል ነዉ ያሉት፡፡

በቀጣይም አገልግሎቱን በሌሎችም አገራት ለማስፋፋት እቅድ እንዳለ ተነስቷል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
አባቱ መረቀ
ሰኔ 03 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.