የሀገር ውስጥ ዜና

አሜሪካ በትግራይ ክልል ለሰብአዊ እርዳታ የሚውል ከ1መቶ 80ሚሊዮን ዶላር በላይ ድጋፍ ማድረጓን አስታወቀች

የአገሪቱ የዕርዳታ ተቋም ዩ ኤስ አይ ዲ እንዳስታወቀው በትግራይ ክልል የተፈናቀሉ ዜጎችን ለመርዳት 1 መቶ 81ሚሊዮን ዶላር የሚያወጡ ቁሳቁሶችን በዛሬው ዕለት ድጋፍ አድርጊያለሁ ብሏል።

ድጋፉ 1መቶ ሺህ ሜትሪክ ቶን የምግብ አይነቶችን እንዲሁም መጠለያ፣ የህክምና ቁሳቁሶችን ያካተተ ስለመሆኑም ተገልጿል ።

በአሜሪካ መንግስት አማካኝነት የተደረገው ይህ ድጋፍ በትግራይ ክልል በከፍተኛ ችግር ውስጥ ለሚገኙ ወገኖች ለመድረስ በማሰብ ነው ተብሏል።

ከምግብ ፣ ከህክምናና ከመጠለያ ድጋፍ በተጨማሪም ለአርሶ አደሮች ዘርና ማዳበሪያ በድጋፉ ተካቷል ነው ያለው ኤጀንሲው ።

ከዚህ ቀደም ዩ ኤስ አይ ዲ 3መቶ 5ሚሊዮን ዶላር የሚያወጡ የተለያዩ ድጋፎችን ማድረጉንም አስታውሷል።

የአሜሪካ መንግስት በትግራይ ክልል ባለው አለመረጋጋት ምክንያት በኢትዮጵያና በኤርትራ ባለስልጣናት ላይ የጉዞ ዕገዳ መጣሉ የሚታወስ ነው።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በአባቱ መረቀ
ሰኔ 03 ቀን 2013

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *