እስከ ዛሬ ድረስ 30 የበይነ መረብ መገናኛ ብዙሀን መመዝገባቸውን የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሀን ባለስልጣን አስታወቀ

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሀን ባለስልጣን የበይነ መረብ መገናኛ ብዙሀን በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ቀርበው ምዝገባ እንዲያካሄዱ ባሳሰበው መሰረት 30 በግለሰብና በተቋም ደረጃ ያሉ የበይነ መረብ መገናኛ ብዙሀን እንደተመዘገቡ ከባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ሰምተናል፡፡

የባለስልጣኑ የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አበራ ወንደሰን ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት የተመዘገቡት የበይነ መረብ መገናኛ ብዙሀን ከ30 ያልፋሉ ነገር ግን ማሟላት ያለባቸውን ዶክመንት ባለማሟላታቸው ጊዜ ተሰጥቷቸዋል ሲሉ ነግረውናል፡፡

የበይነ መረብ መገናኛ ብዙሀን ምዝገባ አስፈላጊነት ስርአት አልበኝነትን ከመቆጣጠር ባለፈ ለመገናኛ ብዙሀኑ የአቅም ማጎልበቻ ድጋፍ ለማድረግ ታስቦ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

በምዝገባው ሂደት ያልተመዘገቡ የበይነ መረብ መገናኛ ብዙሀን ባለስልጣኑ የማያውቃቸውና ተጠያቂነት ሲመጣባቸውም ምንም ድጋፍ አይሰጣቸውም ተብሏል፡፡

የበይነ መረብ አማካኝነት ከውጭ ሀገር የሚተላለፉ መገናኛ ብዙሀን ደግሞ ባለስልጣኑ የቁጥጥር ስራዎችን እያሳደገን ሲመጣ ከውጭ ሀገራት የሚተላለፉ የበይነ መረብ መገናኛ ብዙሀንን የምንቆጣጠርበት አሰራር እንፈጥራለን እንጂ በአሁኑ ወቅት መቆጣጠር አንችልም ብለዋል፡፡

ባለስልጣኑ የበይነ መረብ መገናኛ ብዙሀንን ለማሳደግ ከኢንቨስትመንት ኮሚሽን ከገንዘብ ሚኒስቴርና ብሄራዊ ባንክ ጋር በመነጋገር ላይ መሆኑን ሰምተናል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በመቅደላዊት ደረጀ
ሰኔ 03 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.