የከፍተኛ ትምህርት ጥራትና አግባብነት ኤጄንሲ ለ4 የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የባሉበት ትምህርትን (online Education) ፍቃድ ሰጥቻሁ አለ

ሃላፊው ዶ/ር አንዷለም አድማሴ ‹‹የባሉበት ትምህርት (online Education ትምህርትን በተደራጀ መልኩ ለመስጠት መመሪያ ተዘጋጅቶ ወደ ስራ ከተገበ አጭር ጊዜ ቢሆን ተገቢውን መስፈርት በማሟላታቸው ለ 4 ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተገብቷል ብለዋል።

ስርዓቱ ትምህርት ጥራት ላይ አሉታዊ ተፅእኖ እንዳያሳድር ጠንካራ ስራ እየተሰራ ስለመሆኑ ኃላፊው ተናግረዋል፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በበኩሉ ትምህርት ከመማሪያ ክፍል ወጥቶ ተማሪዎች በያሉበት በራሳቸው የመቀበል ፍጥነት እንዲማሩ ለማድረግ መንግስት በትኩረት እየሰራ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዲኤታ ዶ/ር አህመዲን መሐመድ እንዳሉት
ቴክኖሎጂን በትምህርት ስርዓት ውስጥ በማካተት ተማሪዎችን ከቴክኖሎጂ ጋር ማስተዋወቅ፣ ዜጎች የዲጂታል እውቀት እንዲኖራቸው ማድረግ፣ ባለሙያዎችን ማሰልጠን፣ አስተማማኝ የበይነ መረብ ግንኙነት መሰረተ ልማት መገንባት ላይ እየተሰራ ስለመሆኑም አብራርተዋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ሰኔ 03 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *