ድህነት ለተፅዕኖ እና ለውጭ ጣልቃ ገብነት ስለሚያጋልጥ በራሷ ገቢ የምትተዳደር ሀገር ለመገንባት ከግብር ከፋዮች ጋር ተቀራርቦ መስራት ይገባል ተባለ

ይህን ያሉት የህግ ተገዥነት ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ዘመዴ ተፈራ ሲሁኑ “በአሁኑ ወቅት የሚታየው የሌሎች ሀገራት ተፅዕኖ እና ጣልቃ ገብነት ከድህነታችን የሚመነጭ በመሆኑ ከግብር ከፋዮች ጋር በትብብር በመስራት ወጪዋን በራሷገቢ የምትሸፍን ሀገር መገንባት ይገባል” ብለዋል፡፡

ግብር ከፋዮች እንደ ባህሪያቸው በመለየት የታክስ ህግ ተገዥነት ለማሳደግ የገቢዎች ሚኒስቴር ከሚሰራው ስራ በተጨማሪ የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ እና ትብብር እንደሚያስፍልግ አብራርተዋል፡፡

አለመክፈል ወንጀል መሆኑን እና በአንጻሩ መክፈልን ባህሉ ያደረገ ግብር ከፋይ ይፈጠር ዘንድ ግንዛቤ የመፍጠር ስራን ተጠናክሮ እንዲቀጥል ተገቢ ስራ መሰራት እንዳለበት ተገልጿል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ሰኔ 03 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.