46 ሚሊየን ህጻናት ማህበራዊ ጥበቃ አያገኙም ተባለ፡፡

የተባበሩት መንግስታት የህጻናት አድን ድርጅት (UNCEF) መረጃ እንደጠቆመው በመላው አለም ወደ 46 ሚሊየን የሚጠጉ ህጻናት ማህበራዊ ጥበቃ አይደረግላቸውም ብሏል፡፡

ድርጅቱ ከባለፉት አመታት አንጻር ሲታይ በህጻናት ላይ የሚደርሰው የጉልበት ብዝበዛ በእጥፍ እየጨመረ ይገኛል ሲል አስታውቋል፡፡

በመላው አለም በፈረንጆቹ 2016 ፣ 96 ሚሊዮን የሚሆኑ ህጻናት የጉልበት ብዝበዛ ይደርስባቸው የነበረ ሲሆን አሁን ላይ ግን 160 ሚሊየን ህጻናት ከፍተኛ የሆነ የጉልበት ብዝበዛ እንደሚደርስባቸው ነው መረጃው የጠቆመው፡፡

ከእነዚህ ውስጥም ወደ 46 ሚሊየን የሚሆኑት ደግሞ ምንም አይነት ማህበራዊ ጥበቃ እንደማያገኙ ሪፖርቱ አመላክቷል፡፡

የኮሮና ቫይረስ መከሰቱ ደግሞ ነገሩ እንዲከፋ አድርጎታል ተብሏል፡፡

የጉልበት ብዝበዛ ከሚደረግባቸው ህጻናት መካከል እድሜያቸው ከ11 አመት በታች የሆኑ ህጻናት አብላጫውን ቁጥር እንደሚወስዱ ተገልጿል፡፡

እንደዚሁም እድሜያቸው ከአምስት እስከ 17 አመት የሚሆኑት ደግሞ ለጤናቸው ጉዳት የሚያደርስ ስራ እንዲሰሩ ይገደዳሉ ይላል፡፡

ባለፉት አምስት አመታትም በጉልበት ብዝበዛ ምክንያት 79 ሚሊየን የሚሆኑ ህጻናት የጤና እክል እና የሞራል መላሸቅ እንደገጠማቸው ድርጅቱ ያወጣውን ሪፖርት የሚጠቁመው፡፡

ህጻናት የጉልበት ብዝበዛ ከሚደርስባቸው ዘርፎች ውስጥ የግብርናው ዘርፍ 70 ከመቶ ድርሻ ይወስዳል ተብሏል፡፡

በዚህ ዘረፍ ብቻ 112 ሚሊየን ህጻናት የጉልበት ብዝበዛ ይደረግባቸዋል ሲል የህጻናት አድን ድርጅት አሳስቧል፡፡

ከሰሀራ በታች ባሉ የአፍሪካ፣ የላቲን አሜሪካ ፣የሩቅ ምስራቅ ሀገራት እና የካሪቢያን ሀገራት የህጻናት ጉልበት ብዝበዛ ከፍተኛ እንደሆነ መረጃው ያሳያል፡፡

አልጀዚራ

ሄኖክ ወ/ገብርኤል
ሰኔ 03 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.