በኢትዮጵያ እስካሁን ከ3 ሺህ በላይ የጤና ባለሙያዎች በኮቪድ 19 ተይዘዋል፡፡

የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እንዳለዉ በኢትዮጵያ እስካሁን 3 ሺህ 329 የጤና ባለሙያዎች አገልግሎት እየሰጡ በኮቪድ 19 መያዛቸውን ገልጿል፡፡

የኢንስቲትዩቱ ምክትል ሀላፊ አቶ አስቻለው አባይነህ እንዳሉት፣ አሁን ባለበት ደረጃ ደግሞ 176 የጤና ባለሙያዎች በኮቪድ 19 መያዛቸዉ የተጠቀሰ ሲሆን እስካሁን 36 የጤና ባለሙያዎች ህይወታቸው ማለፋንም ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ በየእለቱ የመመርመር አቅም 14 ሺህ መድረሱ የተገለፀ ሲሆን በቀጣይ ዕቅድ ግን 25 ሺህ ለማድረስ ይሰራል ሲሉ ምክትል ሀላፊው ገልፀዋል።

ህብረተሰቡ ኮቪድ 19 ላይ ያለው የግንዛቤ እያደገ መምጣን የገለጸዉ ኢንስትዩቱ አስታዉቋል፡፡

ለህብረተሰቡ መረጃዉ እንዲደርስ ከማድረግ አንጻርም በሬዲዮ 54 በመቶ ፣ ቴሌቪዥን 47 በመቶ ፣ ማህበራዊ ድህረ -ገፆች 20 በመቶ ከሀይማኖት ተቋማት 5 በመቶ ድርሻ እንዳላቸዉ አቶ አስቻለው ተናግረዋል።

የጤና ሚኒስቴርና የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ያዘጋጁት ትኩረቱን በኮቪድ 19 ያደረገ ሀገር አቀፍ የምርምር ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

ጉባኤው ለሁለት ቀናት የሚዘልቅ ሲሆን ለ15 ወራት በሀገር አቀፋ ደረጃ የኮቪድ ወረርሽኝ ለመከላከል የተሰሩ ስራዎች እንዲሁም ባጋጠሙ ችግሮች ዙሪያ የተሰሩ የጥናት ውጤቶች ይፋ የሚደረግበት ነው።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በረድኤት ገበየሁ
ሰኔ 04 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.