ቻይና በኢትዮጵያ ጉዳዮች የውጭ ጣልቃ ገብነትን ትቃወማለች ብለዋል የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሯ፡፡

የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ይ፤ በኢትዮጵያ ውስጣዊ ጉዳዮች የሚደረግ ጣልቃ ገብነትን አገራቸው እንደምትቃወም መናገራቸው ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዋንግ ይን ጠቅሶ ሲጂቲኤን እንደዘገበው፤ ቻይና በኢትዮጵያ ጉዳዮች የውጭ ጣልቃ ገብነትን ትቃወማለች።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት ከኢትዮጵያው አቻቸው ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ በስልክ ከተወያዩ በኋላ ነው።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩን ዋንግ ይ “ሁለቱ አገራት የሚተባበሩ አጋሮች ናቸው” ብለዋል፡፡

ሲጂቲኤን በድረ ገጹ የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር “ኢትዮጵያ ብሔራዊ ደኅንነትና መረጋጋቷን የመጠበቅ መብት አላት” ማለታቸውን አስነብቧል።

“ኢትዮጵያ ውስጣዊ ጉዳዮቿን በዋነኛነት በራሷ ጥረት መፍታት አለባት ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የኢትዮጵያን ፍቃድ አክብሮ ድጋፍ መስጠት ነው ያለበት ማዕቀብ መጣልም የለበትም” ማለታቸውም ተዘግቧል።

የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከኢትዮጵያው አቻቸው ጋር ባደረጉት የስልክ ውይይት፤ “ቻይና በትግራይ ክልል ያለውን ሰብዓዊ ቀውስ ለማርገብ እርዳታ ለመስጠት ፍቃደኛ ናት የመጀመሪያው ዙር የምግብ እርዳታም ተልኳል” መባሉን ዢንዋ ዘግቧል።

ቻይና በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ያለመግባት ፖሊሲን በማራመዷ አቶ ደመቀ፤ ማመስገናቸውንም ዘገባው አስነብቧል።

ከወራት በፊት በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ውስጥ በትግራይ ክልል የተከሰተውን ቀውስ በተመለከተ ውይይት በተደረገበት ጊዜ የኢትዮጵያ መንግሥትን ደግፈው ከቆሙ አገራት መካከል በምክር ቤቱ ድምጽን በድምጽ የመሻር ሥልጣን ያላት ቻይና አንዷ ነበረች።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በያይኔአበባ ሻምበል
ሰኔ 04 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.