150 ኤጀንሲዎች ፍቃዳቸው ሊሰረዝ እንደሚችል ተነገረ፡፡

ፍቃድ ወስደው ከሚገኙ 314 ኤጀንሲዎች መካከል ከ150 በላይ የሚሆኑት ህጋዊ መንገድ የተከተሉ ባለመሆናቸዉ ስራቸው ሊያቆሙ እንደሚችሉ የሰራተኛ እና ማህበራዊ ሚኒስቴር አስታዉቋል፡፡

የሰራተኛ እና ማህበራዊ ሚኒስትር ምክትል ሀላፊ አቶ ተክሌ ደሬሳ እንደተናገሩት ስራ እንዲያቆሙ የሚደረጉ ኤጀንሲዎች ሀገርን ለችግር ያጋለጡ በወንጀል የተሳተፉ እና በተለያዩ በህገወጥ ተግባራት የተሳተፉ ናቸው ብለዋል፡፡

ፍቃድ ወስደው ስራቸው ሲሰሩ የነበሩት እነዚህ ኤጀንሲዎች ህዝቡን ያለ አግባብ የበዘበዙ ፤የሚያታልሉ እና ሀገር አጥፊዎች ናቸው እንደ አቶ ተክሌ የገለጻ፡፡

የሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚንስቴር በተደጋጋሚ ለተቋሞቹ አካሄዳቸውን እንዲያስተካከሉ ቢያሳውቅም ከድርጊታቸው ሊታቀቡ አልቻሉም ብለዋል፡፡

በዚህም አሁን ላይ በተለያዩ ችግር ውስጥ የገቡ ኤጀንሲዎች ፍቃዳቸው እና ስራቸው እንዲያቆሙ ይደረጋል ተብሏል፡፡

ሚንስቴሩ ኤጀንሲዎች ስራቸውን ባግባቡ መስራት አለመስራታቸው ለማረጋገጥ የተለያዩ ጥናቶች ካደረገ በኃላ ነው ይህንን ለመረጋገጥ የቻለው ሲሉ አቶ ተክሌ ተናግረዋል፡፡

አሁንም ቢሆን በህገወጥ ስራ ላይ የተሰማሩ ኤጀንሲዎች ካሉ አካሄዳቸውን ማስተካከል ይኖርባቸዋል ሲሉ አሳስበዋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ሰኔ 04 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *