የአልጀሪያ የኮምዩንኬሽን ሚኒስቴር የፍራንስ 24 የስራ ፈቃድ መሰረዙ ተሰማ ፡፡

በተደጋጋሚ በግልጽ አልጀሪያን የሚያጠለሹ አሉታዊ ዘገባዎችን እየሰራ ነው ስትል ፍራንስ 24 የተባለው የፈረንሳይ የዜና አውታርን የስራ ፈቃድን ሰርዣለሁ ማለቷን አልጄሪያ አስታውቃለች፡፡

የአገሪቱ የኮምዩንኬሽን ሚንስትሩ እንዳሳወቀው ከሁለት ወር በፊት የዜና ወኪሉ ስለ አልጀሪያ በሚያስተላልፋቸው ዘገባዎች ማስተካከያ እንዲያደርግ ማስጠንቀቂያ ሰጥተው እንደነበር አስታውሰው ፣ በአልጄሪያ የፓርላማ ምርጫ ከተካሄደ ከአንድ ቀን በኋላ እርምጃውን መውሰዳቸውን አስታውቀዋል ፡፡

አንድ የመንግስት ቃል አቀባይ እንዳሉት የፈረንሳይ ዓለም አቀፍ የቴሌቪዥን የዜና አውታር ለአልጄሪያ እና ለተቋሞቿ ግልጽ እና ተደጋጋሚ የጥላቻ ስሜት አሳይቷል ማለታቸውን ቢቢሲ አፍሪካ ዘግቧል፡፡

ፍራንስ 24 በበኩሉ ከአልጀሪያ መንግስት ውሳኔ መደነቁን ገልጾ ሚዲያው ስለ አልጀሪያ ነጻ እና ትክክለኛ ዘገባዎችን ሲሰራ መቆየቱን ገልጿል።

ፈረንሳይ እስካሁን በጉዳዩ ላይ ምንም አይነት አስተያየት አልሰጠችም፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችንቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በያይኔአበባ ሻምበል
ሰኔ 07 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *