ሶማሊያ እና ኬንያ ወደ መደበኛው ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸው ተመልሰዋል

የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ኬንያ ሞቃዲሾ ውስጥ ኤምባሲዋን እንደገና እንድትከፍት ጥሪ አቀርቧል ፡፡

ሶማሊያ በበኩሏ ናይሮቢ ውስጥ ኤምባሲዋን እንደገና እንደምትከፍት ገልጻለች፡፡

በሁለቱ የምስራቅ አፍሪካ ጎረቤቶች መካከል በባህር ድንበር ውዝግብ ምክንያት ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ግንኙነታቸው እየተካረረ መጥቷል፡፡

ሶማሊያ በታህሳስ ወር ከኬንያ ጋር ያላትን ግንኙነት አቋርጣ ነበር፡፡

በኃላም ናይሮቢ በውስጥ ጉዳዮች ጣልቃ ገብታለች በሚል ክስ ማቅረቧን ቢቢሲ አፍሪካ ዘግቧል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችንቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በያይኔአበባ ሻምበል
ሰኔ 08 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *