ቻይና ለኔቶ አባል ሀገራት ስልታዊ እንቅፋት ናት ሲሉ አስጠነቀቁ

በብራሰልስ ለስብሰባ የተቀመጡት የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃልኪዳን ድርጅት (ኔቶ) መሪዎች በቻይና ያጋጥመናል ስላሉት ወታደራዊ ስጋት ውይይት አድርገዋል፡፡

መሪዎቹ ቻይና “ስልታዊ እንቅፋት” ናት ሲሉ አስጠንቅቀዋል፡፡

ቻይና የኒኩለር የጦር መሳሪያዋን በፍጥነት እያሰፋች መሆኗ የወታደራዊ አቅሟን በማዘመን ረገድም ግልፅ ነበረች እንዲሁም ከሩሲያ ጋርም በወታደራዊ ትብብር እያደረገች መሆኑ የስጋታቸው መነሻ መሆኑ ተነግሯል፡፡

የኔቶ አለቃ ጄንስ ስቶልተንበርግ ቻይና በወታደራዊ እና በቴክኖሎጂ ረገድ ወደ ኔቶ “እየቀረበች” እንደሆነ አስጠንቅቀዋል ።

ግን ህብረቱ ከቻይና ጋር አዲስ የቀዝቃዛ ጦርነት ውስጥ መግባት እንደማይፈልግ አጥብቀው ተናግረዋል ።

ኔቶ በ 30 የአውሮፓ አገራት እና በሰሜን አሜሪካ ሀገሮች መካከል የተመሰረተ ጠንካራ የፖለቲካ እና ወታደራዊ ጥምረት ነው።

የተቋቋመውም ከሁለተኛው የአለም ጦርነት በኋላ ሲሆን በተለይም ለኮሚኒስት ስርአት መስፋፋት ስጋት ምላሽ ለመስጠት ያሰበ ነበር ብሏል የቢቢሲ ዘገባ።

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ መሪዎች በዓላማው እና የገንዘብ መዋጮን በተመለከተ ያለመግባባት ውስጥ መግባታቸውን ተከትሎ ጥምረቱ ውጥረት ውስጥ መግባቱ የሚታወስ ነው።

በዶናልድ ትራምፕ የፕሬዝዳንትነት ዘመንም ሀገራቸው ለህብረቱ በምታዋጣው የገንዘብ መጠን ላይ ቅሬታ ሲያሰሙ የቆዩ ሲሆን አሜሪካ የአውሮፓ አገራትን ለመከላከል ያላትን ቀርጠኝነት ጥያቄ ውስጥ የከተተ ነበር።

አዲሱ ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ስልጣኑን ከያዙ ወዲህ የመጀመሪያ የኔቶ ስብሰባ ሲሆን አዲሱ ፕሬዝዳንት ለ72 ዓመቱ ህብረት የአሜሪካን ድጋፍ በድጋሚ ለማሳየት ሞክረዋል።

ባይደን ኔቶ “ለአሜሪካ ፍላጎቶች” ወሳኝ ጠቀሜታ እንዳለው እና አባላት የጥምረቱን የመመሰረቻ ውል አንቀጽ 5 ን በመተግበር እርስ በእርስ ከጥቃት ለመከላከል የተቀመጠውን “የተቀደሰ ግዴታ” እንዲተገብሩ ጠይቀዋል ።

መጪው ረቡዕ ከሩሲያው መሪ ከቭላድሚር ፑቲል ጋር በጄኔቫ ስለሚያካሂዱት ስብሰባ ሲጠየቁ ‹‹ጠንካራ ተፎካካሪ›› ሲሉ ፑቲንን ገልፀዋቸዋል።

በሌላ በኩል ደግሞ ከአፍጋኒስታን የአሜሪካ እና አጋሮቿ ወታደሮቻቸውን ማስወጣታቸውን ተከትሉ የኔቶ መሪዎች የካቡል አየር ማረፊያ እንዲሠራ ለመክፈል መስማማታቸው ተገልጿል ፡፡

የህብረቱ አባል የቱርክ ወታደሮች ከለቀቁ በኋላ አየር ማረፊያውን ለመጠበቅ እና ለማንቀሳቀስ ቃል ገብታለች ፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችንቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በያይኔአበባ ሻምበል
ሰኔ 08 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *