ሱዳን ወደ እርስ በእርስ ጦርነት የመግባት አደጋ አለባት ሲሉ አስጠነቀቁ ጠቅላይ ሚኒስትሯ አብደላ ሀምዶክ

የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ አገሪቱ ወደ ትርምስ እና የእርስ በእርስ ጦርነት ውስጥ የመውደቅ አደጋ አለባት ሲሉ አስጠንቅቀዋል፡፡

ለዚህ ደግሞ ተጠያቂዎቹ የቀድሞ ባለስልጣናት ታማኝ ሰዎች ናቸው ብለዋል እንደ ቢበሲ አፍሪካ ዘገባ፡፡

አሁን አስተዳደራቸው ተግባራዊ እያደረገ ያለው እርምጃዎች ኢኮኖሚውን ለማሻሻል የታሰቡ ናቸው ብለዋል ፡፡

ሰሞኑን በነዳጅ ላይ የሚደረገው ድጎማ መነሳቱን ተከትሎ በአገሪቱ ተቃውሞ ተቀስቅሷል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ሃምዶክ “የፀጥታ ሁኔታው መበላሸቱ በዋናነት በአብዮቱ አካላት መካከል ካለው መበታተን ጋር ተያይዞ በቀላሉ ጠላቶች እና የቀድሞው አገዛዝ አካላት አጋጣሚውን እንዲጠቀሙበት አድርጓል” ሲሉ ተናግረዋል ፡፡

በሱዳን የነበረው የረዥም ጊዜ ግጭት እና እንደ ድርቅና ረሃብ ካሉ የተፈጥሮ አደጋዎች ጋር ተደማምረው የምግብ እጥረት እንዲከሰት ምክንያት ሆኗል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችንቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በያይኔአበባ ሻምበል
ሰኔ 09 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *