በአገረ አሜሪካ ብቻ እስካሁን በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ህይወታቸው ያለፈው ሰዎች ከ6 መቶ አሻቅቧል።
ከዚህ በተጨማሪም አገሪቱ በርካታ ዜጎቿ በኮቪድ የተያዙባት የአለማችን ቀዳሚዋ አገር እንደሆነች የዘገበው ቢቢሲ፣ 33.5 ሚሊዮን አሜሪካውያን በቫይረሱ ተይዘዋል።
የፕሬዝዳንት አስተዳደር እስከ ሃምሌ ወር መጀመሪያ ድረስ 70 በመቶ የሚሆኑ ወጣቶችን እከትባለሁ ቢልም የክትባቱ መዘግየት የሟቾቹ ቁጥር ከፍ እንዲል አድርጎታል ተብሏል።
እስካሁን በአሜሪካ 173 ሚሊዮን ወይንም 52 በመቶ የአገሪቱ ህዝብ የመጀመሪያ ዙር ክትባት ቢወስድም ሁለተኛውን ዙር ክትባት ያጠናቀቁት ግን 43 በመቶ የሚሆኑት ብቻ ናቸው።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ካሊፎርኒያ እና ኒው ዮርክ የእንቅስቃሴ ገደባቸውን በማላላት ሙሉ በሙሉ ክፍት አድርገዋል፡፡
ምንም እንኳን የክትባት ሂደቱ የሰዎችን እንቅስቃሴ በድጋሚ እንዲመለስ ቢያደርገውም እንዲሁም በሃገሪቱ በዚሁ ቫይረስ ሳቢያ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር ቢቀንስም በአሜሪካ በአሁኑ ሰዓት በኮቪድ ጠቅላላ የሟቾች ቁጥር 600,000 መድረሱ ተነግሯል ፡፡
ከአሜሪካ በተጨማሪም ብራዚል 4መቶ 88ሺህ እንዲሁም ህንድ ደግሞ 3መቶ 77 ሺህ ዜጎቻቸውን ለኮቪድ በመገበር ሁለተኛና ሶስተኛ ደረጃን ይዞዋል ።
ቢቢሲ
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችንቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በየዉልሰዉ ገዝሙ
ሰኔ 09 ቀን 2013 ዓ.ም











