ኢትዮጵያ በሳውድ አረቢያ የሚገኙ ዜጎችን እያስወጣች መሆኑ ተነገረ፡፡

በዜጎቹ ላይ እየደረሰ ያለውን እንግልት ለማስቆምና ወደ አገራቸው እንዲገቡ እየተሰራ መሆኑ ተገልጿል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው በሳውዲ የተለያዩ ከተሞች የሚገኙና የመኖሪያ ፍቃድ ባላቸው ኢትዮጵያውያን ጭምር እየደረሰ ያለውን እንግልት እንዲቆምና ዜጎቹ ወደ አገራቸው እንዲገቡ ከአገሪቱ መንግስት ጋር በቅርበት እየሠራ ይገኛል፡፡

የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ሳምንታዊ ጋዜጣዊ መግለጫ እየሰጡ ሲሆን ዜጎችን ከሳውዲ የማሶጣቱ ስራ ተጠናክሯል ነው ያሉት።

ባለፈው ሳምንት 939 ኢትዮጵያውያንን ከሳውዲ ማስወጣት እንደተቻለም አምባሳደሩ አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት ጉዳዩን ከኤምባሲው እና ከአገሪቱ መንግስት ባር በመተባበር በትኩረት እየተከታተለው እንደሆነም አንስቷል ።

በሳውዲ የተለያዩ ከተሞች የሚኖሩና የመኖሪያ ፍቃድ ያላቸውም ጭምር በአገሪቱ መንግስት እንግልት እና እስር እየደረሰባቸው እንደሆነ መናገራቸው አይዘነጋም ።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችንቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በአባቱ መረቀ
ሰኔ 09 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.