የእስራኤል ሀማስ ግጭት ዳግም ስለማገርሸቱ እነተነገረ ነው

እስራኤል በትናንትናው ዕለት በጋዛ የአየር ድብደባ ማካሄዷን ተከትሎ ግጭት መቀስቀሱ ተዘግቧል።

የሃማስ ወታደራዊ ሃይል ተቀጣጣይ ነገሮችን ወደ እስራኤል ምድር በማስወንጨፉ አገሪቱ ድብደባውን እንዳካሄደም የእስራኤል ወታደራዊ ሀይል አስታውቋል።

ወታደራዊ ጦሩ እንዳለው ሃማስ 20 ተቀጣጣይ ነገሮችን በመላክ የሽብር ተግባሩን ሲያካሂድ ነበር ብሏል።

በአየር ጥቃቱ እስካሁን የተጎዱ ዜጎች ይኑር አይኑሩ የሚለው የታወቀ ነገር እንደሌለ የዘገበው አልጄዚራ የሃማስ ቡድን እራሱን እንዲከላከል የቡዱኑ ቃል አቀባይ ጥሪ አቅርበዋል።

እስራኤልና ሃማስ በቅርቡ ለ11ቀናት ጦርነት ከፍተው በኋላ ላይ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ መድረሳቸው አይዘነጋም።

ይሁን እንጂ ሁለቱ ሃይሎች ዳግም ወደ ወደ ለየለት ጦርነት እንዳይገቡ ተሰግቷል ።

በባለፈው ጦርነት 256 ፍልስጤማውያንና 11 እስራኤላውያን ህይወታቸው ማለፉንም ዘገባው አስታውሷል።

አልጀዚራ

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችንቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
አባቱ መረቀ
ሰኔ 09 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *