የ35 አመቱ የስፔን እንደዚሁም የሪያል ማድሪድ ተከላይ ሰርጂዮ ራሞስ በክረምቱ ከክለቡ ጋር እንደሚለያይ አስታውቋል፡፡
በሪያል ማድሪድ ቤት ለረጅም ጊዜያት በአምበልነት ያገለገለው ራሞስ አሁን ወደ ሌላ ክለብ መቀላቀል እንደሚፈልግ አስታውቋል፡፡
ለሪያል ማድሪድ 671 ያህል ጨዋታዎችን ያደረገው ተከላካዩ 101 ያህል ጎሎችን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል፡፡
በተከላካይ ቦታ ከፍተኛውን ጎል ያስቆጠረ ተጫዋች ራሞስ አዲስ ጊዜ በሌላ ክለብ ማሳለፍ እንደሚፈልግ ተናግሯል፡፡
ተጫዋቹ በቀጣይ ወደ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ማቅናት እንደሚፈልግ ተናግሮ ምናልባት የማንችስተር ክለቦች የተጫዋቹ ማረፊያ ሊሆኑ እንደሚችሉ እየተናገረ ነው የሚገኝው፡፡
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችንቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
ሰኔ 10 ቀን 2013 ዓ.ም











