በፖሊስ ይስተዋሉ የነበሩ የገለልተኝነት ጥያቄዎች በዘንድሮ ምርጫ አይደገሙም ሲል የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ

የመዲናዋ ፖሊስ ኮሚሽነር የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮማደር ፋሲካ እንደተናገሩት ከዚህ በፊት በተካሄዱት ምርጫዎች በፖሊስ ላይ ይነሱ የነበሩት የገለልተኛነት ጥያቄዎች በዘንድሮ ምርጫ ላይ እንዳማይነሱ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፡፡

ቀናት በቀሩት አገራዊው ምርጫ ላይ በየምርጫ ጣበያዎች የፖሊስ አካላት እንደሚሰማሩ እና ምርጫው በሰላም እንዲጠናቀቅ ፖሊስ ኮሚሽኑ በቂ ዝግጅት ማድረጉ ለኢትዩ ኤፍ ኤም ገልጸዋል፡፡

ፖሊስ ኮሚሽኑ ከምርጫው ቅስቀሳ እለት ጀምሮ እስከ ምርጫ እለት ድረስ ሊከሰቱ ስለሚችሉ የጸጥታ ችግሮች ለመቅረፍ ጠንካራ ዝግጅት ሲያደርግ እንደነበረ አስታውቋል፡፡

ፖሊስ በዚህ ምርጫ ህግና ስርአት የማስከበር ስራው ላይ ብቻ ትኩረቱን ያደርጋል ብለዋል፡፡

ለዚህም እንዲያግዝ የፖሊስ አካላት የተለያዩ ስልጠናዎች እንደወሰዱም ነግረውናል፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘም የምርጫ ቅስቀሳ ማጠቃለያ በሰላማዊ መንገድ መጠናቁን የተናገሩት ኮማንደር ፋሲካ አጠቃላይ ምርጫ ደግሞ የተሳካ ይሆናል ብለዋል፡፡

ህብረተሰቡ ከወትሮ የተለዩ እንቅስቀሴዎችን በሚመለከትበት ጊዜ ለፖሊስ አካላት ጥቆማ ማድረግ ሲሉ ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችንቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
ሰኔ 10 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.