ባልተጨበጠ መረጃ ሻሸመኔን የትርምስ ቀጠና ለማድረግ የሚሰሩ ሀይሎችን እንደማይታገስ የከተማ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ አስታወቀ

ሻሸመኔ ከተማ ከዚህ ቀደም የተከሰተውን አይነት ትርምስ እና ስርአት አልበኝነት ዳግም ለመፍጠር የሚያስቡ ሀይሎች አስቀድመው ሀሰተኛ መረጃን እያሰራጩ በመሆናቸው ነዋሪው ራሱን ካልተረጋገጠ ወሬ እና አሉባልታ እንዲቆጥብ የሻሸመኔ ከተማ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ሀላፊ አቶ ስንታየሁ ጥላሁን አሳስበዋል፡፡

ከኢትዮ ኤፍ ኤም ጋር ቆይታ ያደረጉት አቶ ስንታየሁ ከተማዋ አሁን ዳግም ወደ ቀደመ እና የሞቀ እንቅስቃሴዋ መመለሷን ተናግረው፡፡

ነዋሪው በስማ በለው የሚነገሩትን ሁሉ እየሰማ መረበሸ የለበትም ብለዋል፡፡

ከተማችን ሻሸመኔ በጣም ሰላም ናት ያሉት አቶ ስንታየሁ ስድስተኛ ጠቅላላ ምርጫም በሰላም እንዲጠናቀቅ የከተማዋ የጸጥታ ሀይል ፤የክልል እና የመከላከያ ሰራዊት በጋራ የቅድመ ጥንቃቄ ስራዎችን ስንሰራ ቆይተናል፣ አሁንም አጠክረን እንቀጥላለን ሲሉ ያክላሉ፡፡

ህዝቡን ለማወከ የሚደረጎ ጥረቶችን እንቅስቃሴዎች በተመለከተ የከተማዋ ነዋሪ ለፖሊስ ጥቁማ እንዲሰጥ ጠይቀዋል፡፡

እኛ የምንሰራው ለህዝቡ ከህዝቡ ጋር ነው ስለዚህ ምንም አይነት ችግር ዳግም በከተማችን አይከሰትም ሲሉ አቶ ስንታየሁ ነግውናል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችንቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በያይኔአበባ ሻምበል
ሰኔ 10 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.