የምርጫ ቦርድ ሃላፊ ብርቱካን ሚደቅሳ የምስጋና መልእክት

እናንት የአገሬ የፖለቲካ ኃይሎች በጠላትነት አልተወዳደራችሁም፤በአደባባይ ዘለፈኝ፥ ስሜን አጠፋ አልተባባላችሁም፤ወይም እኔ አገልጋያችሁ አልሰማሁም።

እንደ አምና ካችአምናው ይቅርታ ካልጠየቀኝ ሞቼ እገኛለሁ፥ ከሱ ጋር ሁለተኛ አልቆምም ያለም የለም።

ለመልካም ፉክክራችሁ ምስጋናዬ ብዙ ነው፤ ቀጣዮቹ የፅሞና ቀናት የበጎነት እና የመልካምነት ጊዜ እንዲሆንላችሁ ስል ይቺን የልቤን መቃተት ላካፍላችሁ ወደድኩ።

ለሞከርናት ትንሽ የጋራ ሙከራ የጎን ውጋት ሆናችሁ ለከረማችሁትም ጭምር፤

ሀገሬ ትንቃ

ህዝቦቹዋም ከፍርሃት ነጻ ሆነው አንገታቸውን ቀና ያድርጉ

በእውቀት ነጻ የወጣንበት

በጠባብ የውስጥ ግድግዳ ያልተከፋፈለ አለም

ቃላት ከእውነት ምንጭ የሚቀዱበት

እጆች ሁሉ በማይታክት ጥረት ወደ ፍጽምና የሚዘረጉበት

ምክንያታዊት ባረጀ ባፈጀ አመለካከትና ጅረት ያልተዋጡበት

አእምሮችን እየሰፋ፣ እየሰፋ ሀሳብና ድርጊታችን በምክንያታዊነት የተዋጀበት
በነጻነት በተሞላው ገነት፣በፈጣሪያችን እቅፍ ሀገሪ ትንቃ!

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችንቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ሰኔ 10 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.