ሰሜን ኮሪያ ከአሜሪካ ጋር ለውይይትም ሆነ ለፍጥጫ መዘጋጀት አለባት ሲሉ ኪም ጆንግ ኡን ተናገሩ፡፡

የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ-ኡን ሀገራቸው ከአሜሪካ ጋር “ለመወያየት አሊያም ለፍጥጫ ” መዘጋጀት አለባት ፤ “በተለይም ለፍጥጫ ሙሉ በሙሉ መዘጋጀት አለባት” ብለዋል፡፡

ፕሬዝደንት ኪም በአዲሱ የባደን አስተዳደር ላይ በቀጥታ አስተያየት ሲሰጡ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው ብሏል ቢቢሲ በዘገባው፡፡

የአዲሱ ፕሬዝደንት ጆን ባይድን አስተዳደር ከስሜን ኮሪያ ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ለመመስረት የሚደረገውን ጥረት ደካማ እንደነበር ዘገባው አስታውሷል፡፡

የሰሜን ኮሪያው መሪ ይህንን መልዕክት ያስተላለፉት በዋና ከተማዋ ፒዮንግያንግ ውስጥ ከአገሪቱ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር ባደረጉት ስብሰባ ላይ ነው፡፡

የገዢው የሠራተኛ ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ በዚህ ሳምንት በመዲናዋ ፒዮንግያንግ ተጀምሯል፡፡

ፕሬዝዳንት ኪም እንዳሉት “የአካባቢያችንን ፤የአገራችንን ክብር እና ነጻ የሆነ የልማት ፍላጎቶቻችንን ለማስጠበቅ ብሎም ሰላማዊ አካባቢን እና የሰሜን ኮሪያን ደህንነት ለማረጋገጥ በተለይ ለሚገጥመን ፍጥጫ ሙሉ ለሙሉ ዝግጁ መሆን አለብን” ማለታቸውን የመንግስት የሆነው የዜና አውታር ኬሲኤን ዘግቧል።

አክለውም ሰሜን ኮሪያ በአካባቢዋ ያለውን ሁኔታ ለማረጋጋትና ለመቆጣጠር “በንቃትና በፍጥነት” ምላሽ ትሰጣለች ሲሉ ተደምጠዋል።

“በኮሪያ ባሕረ ገብ መሬት ላይ ያለውን ሁኔታ በተረጋጋ ሁኔታ ለመቆጣጠር ጥረት እንደምታደርግ” ጨምረው ገልጸዋል፡፡

በሰሜን ኮሪያው መሪና በአዲሱ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት አስተዳደር መካከል ያለው ግንኙነት አሁንም በውጥረት የተሞላ መሆኑ ይነገራል፡፡

ይህ የፕሬዝደንት ኪም አስተያየት የተደመጠው ሀገራቸው ሰሜን ኮሪያ የምግብ እጥረት እንዳጋጠማት ካመኑ ከቀናት በኃላ ነው፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችንቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በያይኔአበባ ሻምበል
ሰኔ 11 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *