ሞሪሺየስ እጅግ ሰላማዊና የተረጋጋች ሀገር ተብላ ተመረጠች

የኢኮኖሚና ሰላም ኢንስቲትዩት የ2021 በአለም አቀፍ ደረጃ በሚገኙ ሀገራት መካከል፤ የሰላምና መረጋጋት መመዘኛዎችን መሰረት አድርጎ ባቀረበው ሪፖርት መሰረት፤ ሞሪሺየስ በአፍሪካ እጅግ ሰላማዊ ሀገር ናት ብሏታል፡፡

ኢንስቲትዩቱ የሰላምና መረጋጋትን መስፈርቶችን መሰረት አድርጎ በ163 በሚሆኑ ሀገራት ላይ በሰራው ጥናት፤ በአፍሪካ ከሞሪሺየስ ቀጥላ ጋና ሁለተኛ ስትሆን ቦትስዋና ደግሞ 3ተኛ ደረጃን በመያዝ በአፍሪካ አህጉር በአመቱ በጣም ጥሩ የሚባል ሰላም የታየባቸው ሀገራት ናቸው ሲል አስቀምጧል፡፡

የአፍሪካ አገራት በዓለም አቀፍ ደረጃ ያላቸው ስፍራ ስናይ ደግሞ ሞሪሺየስ 28ተኛ፤ ጋና 38ተኛ እንዲሁም ቦትስዋና ደግሞ 41ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል፡፡

በዚሁ መመዘኛ መሰረት ከአለም ናይጀሪያ 146ተኛ ደረጃን በመያዝ በአመቱ ሰላምና መረጋጋት የተሳናት ሀገር እንደሆነች የገለጸ ሲሆን ፤ ቶጎ፤ ዑጋንዳ፤ ኬንያ፤የኮንጎ ሪፐብሊክና ካሜሮን ደግሞ በተመሳሳይ ደረጃ ተቀምጠዋል፡፡

በዚሁ ጥናት ውጤት መሰረት አይስላንድ በአመቱ በአለም እጅግ ሰላምና መረጋጋት የነበራት ሀገር ተብላ በአንደኝነት የተመረጠች ሲሆን፤ በአመቱ ሰላምና መረጋጋት ያልታየባት ሀገር ተብላ በመጨረሻ ደረጃ ላይ የቀመጠችው ደግሞ ከየመን፤ ሶሪያ፤ ደቡብ ሱዳንና ኢራቅ ቀጥላ አፍጋኒስታን መሆኗ ታውቋል፡፡

ከነዚህ ሀገራት መካከል አሜሪካ በአመቱ ሰላምና መረጋጋት ካልነበራቸው ሀገራት መካካል ምድብ ውስጥ ተካታለች፡፡

በዋናነት አሜሪካ የጆርጅ ፍሎይ ግድያን ተከትሎ እንዲሁም በካፒታል ህንጻ ላይ የነበረው ህዝባዊ አመጽ የጋጠማት በመሆኗ በአመቱ ጥሬ የሚባል ሰላም ያልነበራቸው ሀገራት ምድብ ውስጥ ተካታለች፡፡

ምንጭ፡ ሲ.ጂ.ቲ .ኤን

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችንቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
ጅብሪል መሐመድ
ሰኔ 16 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *