ሩዋንዳ ጋብቻን ጨምሮ ለኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ከፍተኛ አጋለጭ ናቸው ያለቻቸውን ክስተቶች ለመቆጣጠር እየታገለች መሆኑን አስታውቃለች፡፡
የሃገሪቱ መንግሥት በመግለጫው ክብረ በዓላትን ጨምሮ ሁሉም ዓይነት ማህበራዊ ስብሰባዎች የተከለከሉ ናቸው ሲል አሳስቧል።
በዚህም ባህላዊም ሆነ ሀይማኖታዊ ሰርግን ማድረግ ወይም መደገስ ታግዷል፡፡
ሃገሪቱ ሌሎችንም እገዳዎች ያስቀመጠች ሲሆን እንደ አካላዊ እርቀትን መጠበቅ ፣ የፊትና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል ማድረግን ጨምሮ ሌሎችንም ወረርሽኙን ለመከላከል የሚረዱ መመሪያዎች በጥብቅ ይተገበራሉ ብሏል መግለጫው፡፡
13 ሚሊዮን ህዝብ እንዳላት የሚነገርላት ሩዋንዳ፣ ወረርሽኙ ከተከሰተ ጀምሮ በአጠቃላይ 31 ሺህ 435 ዜጎቿ በኮሮና ሲያዙባት 388 ሰዎች ደግሞ ለሞት ተዳርገዋል፡፡
ሃገሪቱ ምንም እንኳን እስከ መጪው የፈረንጆች አዲስ ዓመት ድረስ 60 ከመቶ የሞሆነዉን ህዝቧን ለመከተብ እቅድ እንዳላት ብትገልጽም እስካሁን ክትባቱን ያገኘው ህዝብ ግን ሶስት በመቶ ብቻ መሆኑን AFP ዘግቧል፡፡
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በየዉልሰዉ ገዝሙ
ሰኔ 16 ቀን 2013 ዓ.ም











