አየር መንገዱ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቀው ከአዲስ አበባ ወደ አስመራ የተቋረጠው በረራ በዛሬው ዕለት ይጀምራል።
የአየር መንገዱ የኮሙኒኬሽን ባለሙያ አቶ ሄኖክ ሲራክ እንደነገሩን በረራው በኮቪድ ምክንያት መቋርጡን አስታውሰዋል ።
አየር መንገዱ ከዛሬ ማለትም ከሰኔ 16 2013 ዓ.ም ጀምሮ ወደ አስመራ መብረረ ይጀምራል ነው ያሉት።
የኮቪድ 19 መከሰቱን ተከትሎ ወደተለያዩ አገራት ይደረግ የነበረው በረራ መስተጓጎሉ አይዘነጋም ።
ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ከ20 አመታት ውጥረትና ኩርፊያ በኋላ በመታረቃቸው አየር መንገዱ አገልገሎት መጀመሩ ይታወሳል ።
ይሁን እንጅ ሁለቱ አገራት ከታረቁ በኋላ ድንበሮቻቸውን ከፍተው የነበረ ቢሆንም ወዲያውኑ መዝጋታቸው ይታወቃል ።
ከዚህ ባለፈም የኤርትራ ወታደሮች በትግራይ ክልል እንደሚገኙና የሁለቱ አገራት መሪዎች ወታደሮቹ በቅርቡ ይወጣሉ ብለው ተናግረው የነበረ ቢሆንም አሁን ግን ሙሉ በሙሉ ስለመውጣታቸው የሚታወቅ ነገር የለም ።
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በአባቱ መረቀ
ሰኔ 16 ቀን 2013 ዓ.ም











