ፑቲን ዩክሬን ውስጥ በ2014 ‘መፈንቅለ መንግስት’ በማቀናጀት አሜሪካን ከሰዋል::

የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የቀድሞው የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቪክቶር ያኑኮቪች ከስልጣን እንዲባረሩ በፈረንጆቹ በ2014 የተካሄደው ህዝባዊ አመጽ በአሜሪካ የተቀናበረ እና በዋሽንግተን የአውሮፓ አጋሮች የተደገፈ እንደነበር ተናግርዋል።

በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ጀርመን ሶቪዬት ሕብረትን የወረረችበትን 80ኛ ዓመት ለማክበር በጀርመን ጋዜጣ ላይ አንድ በወጣ ጽሑፍ፣ የያንኮቪች መነሳት “ፀረ-ሕገ-መንግስታዊ እና የተቀናጀ መፈንቅለ መንግስት” በማለት ገልፀዋል ፡፡

የክሬምሊን ደጋፊ የሆኑት የዩክሬኑ መሪ ያንኮቪች ከተወገዱ ወዲህ ከጎረቤት ሩሲያ ጋር ውዝግብ ተቀስቅሷል።

ሞስኮ ዩክሬን ውስጥ አሜሪካ ሁከት እና ብጥብጥ ለማስነሳት ሞክራለች ስትል ለረዥም ጊዜ ስትከስ ቆይታለች፡፡

ከየካቲት 2014 በኋላ ሩሲያ የጥቁር ባሕር ክሪሚያ አካባቢን በመቀላቀል በዩክሬን ምሥራቅ የትጥቅ ግጭት ሲነሳ ለተገንጣይ ተዋጊዎች ድጋፍ ሰጥታለች ይባላል፡፡

ከቀዝቃዛው ጦርነት በኋላ አገራት ከምዕራቡ ዓለም ወይም ከሩስያ ጎን በመሰለፍ መካከል “ሰው ሰራሽ ምርጫ” እንዲገጥማቸው ያደረጋቸው “የዩክሬይን አሳዛኝ ሁኔታ” እንደነበረው ፑቲን ጽፈዋል።

“አሜሪካ መፈንቅለ መንግስትን ለምን አዘጋጀች ፣ የአውሮፓ ሀገሮች ለምን ይደግፉታል ፣ ይህ እራሱ በዩክሬን መከፋፈል እና ክራይሚያ የመነጠል ፍላጎትን አስነሳ“ ማለታቸዉን አልጀዚራ ዘግቧል።

“አሁን የመላው አውሮፓ ደህንነት ስርዓት በከባድ ሁኔታ ወርዷል ፡፡ ውጥረቱ እየጨመረ መጥቷል እናም አዲስ የመሳሪያ ውድድር አደጋዎች እውን እየሆኑ ነው“ ሲሉ አክለዋል።

ፑቲን የሰጡት አስተያየት የተነበበው ባለፈው ሳምንት ከአሜሪካው አቻቸው ጆ ባይደን ጋር በጄኔቫ ውይይት ማድረጋቸውን ተከትሎ ነው።

ሁለቱ ሰዎች በውይይታቸው በወደፊቱ የጦር መሣሪያ ቁጥጥር ስምምነቶችን በተመለከተ መሠረት ለመጣል እና የየራሳቸውን አምባሳደሮች ወደ ሥራዎቻቸው ለመመለስ ቃል መግባታቸው የሚታወስ ነው፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችንቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ሰኔ 16 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.