የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ጋዜጣዊ መግለጫ እየሰጡ ነዉ፡፡
ቃል አቀባዩ እንዳሉት፣በሳውዲ የሚገኙ ዜጎች ጉዳይ በ2 ሳምንት ውስጥ ምላሽ ያገኛል።
በሳውዲ አረቢያ በሚገኙ ዜጎች ላይ የሚደርሰውን እንግልትና ስቃይ ለማስቆምም የተለያዩ ባለድርሻ አካላት የተካተቱበት ግብረ ሃይል ተቋቁሞ ሥራውን እንደጀመረ ገልፀዋል።
ይህ ግብረ ሀይል በሳውዲ አረቢያ ያሉ ዜጎችን ሙሉ በሙሉ በቀጣዮቹ 2 ሳምንታት ወደ አገራቸው ይመልሳል ተብሎ እንደሚጠበቅም ቃል አቀባዩ አስታውቀዋል ።
ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በሳውዲ ያሉ ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ እንግልትና እስር እየገጠማቸዉ መሆኑን ዜጎቹ በተደጋጋሚ መናገራቸው ይታወሳል።
ባለፈው ሳምንት ዜጎቹ ያሉበትን ሁኔታ ለመመልከት የልዑካን ቡድን ወደ ሪያድ ማቅናቱንም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ማሳወቁ አይዘነጋም።
ይህንንም ችግር በዘላቂነት ለመፍታት በቀጣዮቹ 15 ቀናት ዜጎቹን ሙሉ በሙሉ ወደ አዲስ አበባ የመመለስ ስራ እንደሚከናወን አምባሳደር ዲና አስታውቀዋል።
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በአባቱ መረቀ
ሰኔ 17 ቀን 2013 ዓ.ም











