‹በ12 ዓመት ውስጥ በናይጄሪያ ከ 300 ሺህ በላይ ህፃናት በግጭት ምከንያት ተገድለዋል ››ሲል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሪፖርት አመላከተ

በምዕራብ አፍሪካ የምትገኘው ሀገር ናይጄሪያ በሰሜንናዊው ምስራቅ አካባቢዋ በአክራሪው ቦኩሃራም ጥቃትን ጨምሮ ቀጥተኛም ይሁን ቀጥተኛ ባልሆነ ጥቃት ከ300 ሺህ በላይ ህፃናት ለህልፈት እንደተዳረጉባት ሪፖርቱ ያመላክታል፡፡

በአካባቢው ከ 350 ሺህ በላይ ነዋሪዎች መሞታው የተገለፀ ሲሆን ከነዚህም አብዛኛውን ቁጥር የሚይዙት ከ 5ዓመት በታች የሆኑ ህጻናት ናቸው ብሏል፡፡

በዩኤን ሪፖርት እንደተመላከተው 350 ሺህ ከሚሆኑት ዜጎቿ ውስጥ 314 ሺህ የሚሆኑት ቀጥተኛ ባልሆነ ምክንያት ህይወታቸው እንዳለፈ ተገልጿል፡፡

በአዲሱ ጥናት ላይ በተጨማሪ የተመላከተው የሃገሪቷ ህዝብ የፀጥታ ስጋት፣ የስራ አጥነት እና የኑሮ መናር፣ በአማፅያን መጠቃት ተደማምሮ ህዝቡን ወደ አደባባይ እንዲወጣ እያረገው ነውም ተብሏል፡፡

የአልጄዚራ ዘገባ በፈረንጆቹ አቆጣጠር በ2009 ዓ.ም በአክራሪው ቦኩሃራም ከ 2 ሚሊዮን በላይ ዜጎች መገደላቸውን አስታውሷል፡፡

ረድኤት ገበየሁ
ሰኔ 18 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *