አፍሪካ በኮቪድ-19 ምክንያት 190 ቢሊየን ዶላር ኪሳራ እንደደረሰባት ተገለጸ።

የ ኮቪድ-19 ወረርሽኝ በአፍሪቃ ኢኮኖሚ ላይ 190 ቢሊዮን ዶላር ኪሳራ አስከትሏል ሲሉ የአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት አኪንዊሚ አዲሲና በአመታዊው የአፍሪካ ልማት ባንክ ስብሰባ ተናገሩ፡፡

ፕሬዝደንቱ እንዳሉት ወረርሽኙ 30 ሚሊዮን ሰዎችን ወደ ድህነት አዘቅት እንደከተታቸው በመግለጽ በ 2021 መጨረሻ ላይም 39 ሚሊዮን የሚገመት ህዝብ የከፋ ድህነት ውስጥ ሊኖር እንደሚችል ጠቁመዋል፡፡

ሆኖም በዓለም አቀፍ የካፒታል ገበያዎች ላይ የ 3 ቢሊዮን ዶላር የማኅበራዊ ተጽዕኖ ቦንድ በመጀመሩ በአፍሪካ ኢኮኖሚ ውስጥ ፈጣን እድገት ታይቷል ብለዋል፡፡

ባንኩ የ10 ቢሊዮን ዶላር የቀውስ ወቅት ምላሽ መስጫ ተቋምንም ይፋ ማድረጉን አዲሲና አስታውቀዋል ፡፡

ለአፍሪቃ የበሽታ መከላከል ማዕከል 28 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አድርገናል ፡፡ ህይወትን እና ኑሮን አድነናል ሲሉም ተደምጠዋል እንደ አናዶሉ ዘገባ ፡፡

በተጨማሪም በ 2021 አማካይ የታቀደው አጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት (ጂዲፒ) 3.4 በመቶ መሆኑን አንስተው በመሆኑም ይህንን ዕድገት በማስመዝገብ አህጉሪቱ እንድታገግም እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ያይኔአበባ ሻምበል
ሰኔ 18 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.